12th August 2015

የመጋቢያን ኮንፍረንስ 3ኛ ቀን

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የ2014 ዓ.ም የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ መታሰቢያ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያዘጋጀው የጸሎት እና የምልጃ መርሃግብር ተካሂዷል። የተለያዩ መንፈሳዊ ዝማሬዎች በተለያዩ ዘማሪያን በቀረቡበት በዚህ መርሃ ግብር ላይ የኅብረቱ ፕሬዚዳንት መጋቢ ፃድቁ አብዶ፣ የወንጌሉ ዋነኛ እምብርት የክርስቶስ ሞት፣ መቀበርና በሦስተኛው ቀን መነሳት መሆኑን ከመልእክታት ጠቅሰው፣ በትንሳሣኤውም አድመኝነት፣ ቅናት፣ በቀል፣ ጥላቻና ቂም መወገዱን በመግለጽ በዚህ የትንሣኤ መንገድ መመላለስ እንደሚገባ አሳስበዋል። በዝግጅቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የመልካም ምኞት መግለጫ ካስተላለፉ በኋላ፣ ትንሣኤ መከራንና ተስፋ መቁረጥን በአሸናፊነት መወጣትን የሚያመለክት የድል በዓል እንደሆነ ገልጠው፣ የትንሣኤ መንገድ የፍቅርና የመሥዋዕትነትን ዋጋ የሚጠይቅ እንደመሆኑ፣ ለመጪው ትውልድም ትንሣኤ ይሆን ዘንድ በተመሳሳይ ጎዳና ማለፍ ከእያንዳንዳችን ይጠበቃል። እርስ በእርስ ለመቀራረብ፣ ለመመካከርና ልብ ለልብ ተገናኝቶ የሌሎችን ሕመም ለመታመም የትንሣኤን ልብ ይጠይቃል፤ ያኔ ጥረታችንና ድካማችን ውጤታማ ይሆናልል በማለት ተናግረዋል። የጥንቷ ቤተ-ክርስቲያን የክርስቶስን ትንሣኤ በታላቅ ግለት ታውጅ እንደነበር በመግለጥ መልዕክታቸውን የጀመሩት ፓስተር ጌቱ አያሌው፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ በጥያቄ ለተሞሉ ልቦች ምላሽ እንደሰጠ፣ ዛሬም በማናቸውም ሁኔታ በግል፣ በቤተሰብና በሀገር ደረጃ ለሚያጨንቁን ጉዳዮች ሞትን ድል የነሳውና ሕያው የሆነው ጌታ ትንሣኤን ይሰጠናል፤ ሆኖም ወደ እርሱ ለመቅረብና በፊቱም ለመቆም አቅም እንድናገኝ ወደ ቃሉ መመለስና ፊቱንም በጸሎት መፈለግን መማር ይኖርብናል፤ ያን ጊዜ ልቦናችን ይበራል፣ አእምሮአችን ይከፈታል፣ ሸክማችን ይራገፋል፣ በጥያቄ የተሞላ ልብና በጥያቄ የተሞላች አገር ይዘን መጓዛችን ያበቃል፤ ትንሣኤም ይሆንልናል ሲሉ ቃለ እግዚአብሔርን አካፍለዋል። በመጨረሻም እግዚአብሔር ፊቱን እንዲመልስልን፣ የሕዝባችንን ሰቆቃ እንዲያነሳ፣ ጨለማውን ገፎ ብርሃኑን እንዲያበራልንና ምድራችንን እንዲፈውስ ጸሎት ተደርጎል። በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያዘጋጀው የጸሎት እና የምልጃ መርሃግብር ተካሂዷል። ይሰጠናል፤ ሆኖም ወደ እርሱ ለመቅረብና በፊቱም ለመቆም አቅም እንድናገኝ ወደ ቃሉ መመለስና ፊቱንም በጸሎት መፈለግን መማር ይኖርብናል፤ ያን ጊዜ ልቦናችን ይበራል፣ አእምሮአችን ይከፈታል፣ ሸክማችን ይራገፋል፣ በጥያቄ የተሞላ ልብና በጥያቄ የተሞላች አገር ይዘን መጓዛችን ያበቃል፤ ትንሣኤም ይሆንልናል ሲሉ ቃለ እግዚአብሔርን አካፍለዋል። በመጨረሻም እግዚአብሔር ፊቱን እንዲመልስልን፣ የሕዝባችንን ሰቆቃ እንዲያነሳ፣ ጨለማውን ገፎ ብርሃኑን እንዲያበራልንና ምድራችንን እንዲፈውስ ጸሎት ተደርጎል። በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያዘጋጀው የጸሎት እና የምልጃ መርሃግብር ተካሂዷል።ይሰጠናል፤ ሆኖም ወደ እርሱ ለመቅረብና በፊቱም ለመቆም አቅም እንድናገኝ ወደ ቃሉ መመለስና ፊቱንም በጸሎት መፈለግን መማር ይኖርብናል፤ ያን ጊዜ ልቦናችን ይበራል፣ አእምሮአችን ይከፈታል፣ ሸክማችን ይራገፋል፣ በጥያቄ የተሞላ ልብና በጥያቄ የተሞላች አገር ይዘን መጓዛችን ያበቃል፤ ትንሣኤም ይሆንልናል ሲሉ ቃለ እግዚአብሔርን አካፍለዋል። በመጨረሻም እግዚአብሔር ፊቱን እንዲመልስልን፣ የሕዝባችንን ሰቆቃ እንዲያነሳ፣ ጨለማውን ገፎ ብርሃኑን እንዲያበራልንና ምድራችንን እንዲፈውስ ጸሎት ተደርጎል። በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያዘጋጀው የጸሎት እና የምልጃ መርሃግብር ተካሂዷል።